🔢 የግዕዝ ቁጥሮች እና ተዛምዷቸው (Ge'ez Numbers)

የግዕዝ ቁጥሮች ጥንታዊ የኢትዮጵያ የቁጥር ስርዓት ሲሆኑ፣ ከ1 እስከ 10,000 ያሉ ቁጥሮችን በራሳቸው ምልክቶች ይገልጻሉ።

ውጤት
—

ምሳሌ፦ ፳፻፲፱ = ፳ × ፻ (2,000) + ፲፱ (19) = 2019። ፩ ከ፻ እና ከ፼ በፊት አይጻፍም (100 = ፻፣ 10,000 = ፼)።

1. አንደኛ ቁጥሮች (1 - 10)

ምልክትአነባበብየዓረብኛ ቁጥር
፩አሐዱ1
፪ክልኤቱ2
፫ሠለስቱ3
፬አርባዕቱ4
፭ሐምስቱ5
፮ስድስቱ6
፯ሰብዐቱ7
፰ስምንቱ8
፱ተሠዐቱ9
፲ዐሠርቱ10

2. አስሮች (20 - 90)

ምልክትአነባበብየዓረብኛ ቁጥር
፳እሥራ20
፴ሠላሳ30
፵አርብዓ40
፶ሐምሳ50
፷ስድሳ60
፸ሰብዓ70
፹ሰማንያ80
፺ተሠዓ90

3. መቶዎች እና ሺዎች

ምልክትአነባበብየዓረብኛ ቁጥር
፻ምዕት100
፼እልፍ10,000
የግዕዝ ቁጥሮች ኢትዮጵያን ያስሱ 🇪🇹 ብሎግ አግኙን እና ይከተሉን ስለ እኛ